ዜጎች ለማህበራዊ ፍትህ ዓለም አቀፍ ካውንስል
Citizens for Social Justice International Council (CSJIC) - USA Region

ዜጎች ለማህበራዊ ፍትህ አለምአቀፍ ካውንስል /CSJIC

ተልእኳችን ኢትዮጵያ ውስጥ ዜግነትን መሠረት ያደረገ ዴሞክራሲያዊ የፖለቲካ ስርአት እንዲጎለበት ማገዘ፤ የህዝባችን ሁለንተናዊ ችግሮች እንዲቃለሉ የበኩላችንን አስተዋጽኦ ማበርከትና በትውልድ ሀገራችን የወደፊት አቅጣጫ ላይ በጎ ሚና መጫዎት ነው።  

Our mission is to support the formation of citizenship-based democratic political order in Ethiopia, contribute to the alleviation of multi-faceted problems of our people and play constructive roles in the future direction of our country of origin.

አባል ይሁኑ

አባል በመሆን ዜግነትን መሰረት ያደረገ ዲሞክራሲያዊ ስርአት በኢትዮጵያ እንዲመሰረትና የህዝባችን ዘርፈ ብዙ ችግሮች ተቃለው ማህበራዊ ፍትህ በሀገራችን እንዲሰፍን የበኩለዎን ድርሻ ይወጡ።

በተላከልዎ የምዝገባ ኢሜል መሰረት እንዴት ድህረ ገፃችን ውስጥ ገብተው የአባልነት ክፍያዎን መፈጸም እንደሚችሉ የሚይሳይ

  1. የአፈጻጸም መመሪያ ቪዲዮ (ዴስክቶፕ ኮሚፒተር ሲጠቀሙ)
  2. የአፈጻጸም መመሪያ ቪዲዮ (ስማርት ፎን ሲጠቀሙ) 

Become a member

Get involved to support the formation of citizenship-based democratic political order in Ethiopia and contribute your part for the alleviation of multi-faceted problems of our people.

Join us

የዜጎች ለማህበራዊ ፍትህ አለምአቀፍ ካውንስል እሴቶች

እሴቶቻችን ተልእኳችንን በተሳካ ሁኔታ ለመፈጸምና ራዕያችንን ለማሳካት የምንገለገልባቸው የሀሳብና የድርጊት መርሆቻችን ናቸው። 
  • የሃላፊነትና የተጠያቂነት ስሜት፤ ሀሳቦቻችንና ድርጊቶቻችን በሃላፊነትና ተጠያቂነት ስሜት ይመራሉ።
  • ተቆርቋሪነትና አካታችነት፤ ለሁሉም ኢትዮጵያዊያን እኩል እንቆረቆራለን፤ እንቅስቃሴያችን ለማንም የማያደላ ሁሉን አካታች ይሆናል።
  • ስራ ወዳድነትና ታታሪነት፤ ለራሳችን የሰጠነው ስራ ታላቅ መሆኑን እናምናለን፤ ካሰብነው ግብ ለመድረስ ስራ ወዳድነትና ታታሪነት ቁልፍ መሆናቸውን እንቀበላለን።
  • ፋይዳ ፈላጊነትና ትልቁን ስእል ተመልካችነት፤ አቅማችንን ሁሉ ፋይዳ ባለው ጉዳይ ላይ እናውላለን፤ ሀሳቦቻችን፣ ድርጊቶቻችንና ግንኙነቶቻችን ሁሉ የሚመሩት ትልቁንና ዋናውን የጋራ አላማ ታሳቢ በማድረግ ነው።
  • ዘመንተኝነትና ስልጡንነት፤ ሀሳቦቻችንና ድርጊቶቻችን ዘመኑን የሚመጥኑና በእውቀት ላይ የተመሰረቱ ይሆናሉ።
  • መልካም አሳቢነት፣ ቅንነትነትና ሀቀኝነት፤ ለበጎ ተግባር እንተጋለን፤ ነገሮችን ሁሉ በቅንነት እንመዝናለን፤ ለእውነት እንቆማለን።
  • ንቁነትና አስተዋይነት፤ የሁኔታዎችን መንሰኤና ውጤት ለመገንዘብ ሁሌም እንጥራለን፤ ሀሳቦቻችንና ድርጊቶቻችን ወደምንፈልገው ግብ የሚያስጠጉን መሆናቸውን በጥንቃቄ እንመረምራለን።

ዜጎች ለማህበራዊ ፍትህ አለምአቀፍ ካውንስል በዪናይትድ ስቴትስ ቨርጂኒያ ግዛት ውስጥ የተቋቋመ ግብረ ሰናይ ድርጅት ነው።

Citizens for Social Justice International Council (CSJIC) is a not-for-profit organization incorporated in the state of Virginia, USA.

Powered by Wild Apricot Membership Software